®
speaker
Virtual
Great • Alfred • Nobel • Gives • Aspiration!
Nobel & Laureates' Ideas & Thought Processes!
Know Thyself Video

Alfred Nobel Video

501(C)3
Nonprofit Organization

Buffet, Gates, French Advice

Translated to Amharic by Yordanos Mengistu

ቡፌት፣ ጌትስ፣ የፍሬንች ምክር

emanual

ኢማኑኤል ኖቤል፣ “አስፈጻሚው የሟች ነፍስ ቃል አቀባይ ነው!

ማውጫ

 1. ማሪ ከኢማኑኤል ኖቤል የተማረችው
 2. ዋረን ቡፌት፣ ቢል ጌትስ እና ሜሊንዳ የህንድ ሀብታሞች በጎ አድራጎትን እንዲያደርጉ የመከሩት ምክር
 3. የማሪ የክርስትና አያቶች እና አባት
 4. የማሪ አድሏዊ እናት
 5. የማሪ አድሏዊና ወንጀለኛ ወንድሞች
 6. አድሏዊ የሆኑት ወንድሞቿ የአባታቸውን የእርሻ መሬት በሕገወጥ መንገድ ሸጡ ከዚያም በተጨማሪ ማሪ የሚገባትንም ድርሻ በስግብግብነት ወስደዋል
 7. ማሪ
 8. ወንጀለኛ ወንድሞቿ ማሪን በኬሮሲን ለማቃጠል ሞከሩ
 9. ወንጀለኛ ወንድሞቿ ማሪ እንድትሞት ይፈልጋሉ
 10. ወንጀለኛ ወንድሞቿ ማሪን በቢላ ሊወጉ ሞከሩ ከዛም ያለማቋረጥ ያስቸግሯት ነበር
 11. ።ወንጀለኛ ወንድሞቿ በራሷ ሴት ልጅ ከምትታገዝ ተከታታይ ገዳይ ጋር በማሴር ማሪ ጥቃት እንዲደርስባት አድርገዋል ።የወንጀለኛዋ ባሏም ያለማቋረጥ ማሪን ይከታተላታል።
 12. ወንጀለኛ ወንድሞቿ ማሪን ለመግደል ወንጀለኛ ከሆነው የማሪ ማርሻል አርት አስተማሪ ጋር አሴሩ ።
 13. ወንጀለኛ ወንድሞቿ በሕገ-ወጥ መንገድ የአባታቸውን እናት የሩዝ ማሳን እና ቤት ሸጡ እናም ማሪን የሚገባትንም ድርሻ በስግብግብነት ወስደዋል
 14. ወንጀለኛ ወንድሞቿ የማሪን ኮከብ ወደ አስደናቂው ኮከብ ቆጣሪ ላኩ
 15. የማሪ ሳይንሳዊ ምርምር ለማድረግ ያላት ህልም
 16. የማሪ ቅድመ አያቶቿን ለማክበር የምታደርገው ጥረት እና ምኞታቸውን ለማሟላት የምታደርገውበጎ አድራጎት
 17. ማጠቃለያ
 18. የማሪ የእናቷ እናት ለማሪ እውነቱን ተናገረች
 19. ተከታታይ ገዳይ የሆነችው እና ሴት ልጇ ለዓመታት ብዙ ሰዎችን ለመግደል ሙከራ አድርገዋል
 20. የወንጀለኛ ወንድማሞች ስግብግብነት

ማሪ ከአማኑኤል ኖቤል የተማረችው

bubble

አልፍሬድ ኖቤል

ኢማኑኤል ኖቤል፣የ አልፍሬድ
ኖቤል ተወዳጅ የወንድም ልጅ

ራግናር ሶልማን,ለ አልፍሬድ ኖቤል
26 ዓመት ረዳት እና
የውርሱ አስፈፃሚ።

[የኖቤል] ሽልማቶችን በተመለከተ በአልፍሬድ ኖቤል ኑዛዜ ውስጥ ያለው አንቀፅ ህጋዊ ጉድለት ያለበት ነበር። ስለዚህም ኑዛዜውን ተግባራዊ ለማድረግ ፈጽሞ የማይቻል ነበር. በሩሲያ የሚኖረው የአልፍሬድ ኖቤል ተወዳጅ የወንድም ልጅ ኢማኑኤል የኖቤል ፍላጎት እንዲከበር ፈልጎ ነበር። ኢማኑኤል የኖቤል ኑዛዜ አስፈፃሚ ለሆነው ራግናር ሶልማን በ ሩሲያ ህግ ኑዛዜ ፈጻሚ የተናዛዡ “የነፍስ ቃል አቀባይ” መሆኑን ነግሮታል።

ዋረን ቡፌት፣ ቢል ጌትስ እና ሜሊንዳ የህንድ ሀብታሞች በጎ አድራጎትን እንዲያደርጉ የመከሩት ምክር

bubble

ዋረን ቡፌት ምስል፡ ማርክ
ሂርሼይ/ዊኪ

ቢል ጌትስ ምስል፡ ራስል
ዋትኪንስ/ዲፊድ/ዊኪ

ሜሊንዳ ፈረንሳይኛ. ምስል: ዓለም
የኢኮኖሚ መድረክ / ዊኪ

ህንድ በበጎ አድራጎት መዝገብ ግርጌ ላይ ስትገኝ በሙስና ዝርዝር ደሞ አናት ላይ ትገኛለች። የሌላ ሀገር በጎ አድራጊዎች ወደ ህንድ ሄደው ሀብታም ህንዶች በጎ አድራጎት እንዲሰሩ መምከራቸው አሳፋሪ ነው።

የሚከተለው እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ታሪኩም ፕሮፌሽናል ዲግሪ ያላቸው ሶስት ሀብታም ወንድማማች ቤተሰብ አንድ ጥሩ እና በጎ አድራጎት የሚሰሩ ቅድመ አያቶቿን ለማክበር እና በጎ አድራጎት ለመስራት የምትፈልግ እህታቸውን ማሪን ለመግደል ብዙ ሙከራዎችን ሲያረጉ ያሳያል። ወንድሞቿ በስግብግብነት የሚገባትን ብዙ ውርስ ወስደዋል። ይህ ታሪክ ስለ አንዲት ሴት ከጥላቻ እና ከጥቃት ጋር ብትጋፈጥም ያላትን ጀግንነት እና ሌሎችን ለመርዳት የምታረገውን ጥረት ያሳያል ። ይህ ታሪክ በህንድ እና በሌሎች የአለም ክፍሎች በጣም የተለመዱ አመለካከቶችን ያሳያል።

የማሪ የክርስትና አያቶች እና አባት

bubble

በጎ አድራጊ ሟችአባት

በጎ አድራጊ ሟች የሴት አያት

በጎ አድራጊ ሟች የወንድ አያት

በጎ አድራጊ ሟች የሴት አያት

የአያቶቻቸው እና የአባቶቻቸው ንብረት በቅንነት የተገኘ ሲሆን እና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የህንድ ሩፒ ነው። አባትየው በከተማው ውስጥ ትልቅ የሚያምር ቤት እና በከተማ ዳርቻዎች የእርሻ መሬት ነበረው; የአባታቸው እናት በመንደሩ ውስጥ የሩዝ ማሳ እና ቤት ነበሯት ።የእናታቸው ቤተሰቦች በከተማ ውስጥ ትልቅ ቆንጆ ቤት ነበራቸው። ወርቅ፣ ብር፣ ገንዘብ፣ ወዘተ ነበራቸው።በእኩልነት፣ በበጎ አድራጎት እና በጎ አድራጎት መርሆች ያምኑ ነበር እናም ሀብት ምንም ከሌላቸው ጋር መካፈል እንዳለበት ያምኑ ነበር።

የማሪ አድሏዊ እናት

የማሬ አባት ሲሞት ንብረቱ በእናትየው ስም ተላልፏል። እናትየው ለወንድ ልጆቿ ታዳላለች የገዛ ልጇንም ማሪ በውርስ ያገኘችውን የሚገባትን ድርሻ ከልክላታለች። የእናትየው እምነት ሀብቱ ለወንድ ልጆቿ እና ለቤተሰቦቻቸው ብቻ መሰጠት እንዳለበት ነበር። የራሷን ወላጆች፣ የባሏን እና አማቾች ሀሳብ አልተጋራችም። ያደገችው ትልቅ ፍቅር እና አክብሮት ባላቸው ወላጆች ነው ። ወላጆቿ ሁለቱንም ወንድ እና ሴት ልጆቻቸውን እሷንም ጨምሮ በጥሩ ሁኔታ ይንከባከቡ ነበር እና ወንድ ልጆቻቸውን እህቶቻቸውን እንዲያከብሩ አድርገው ነበር ያሳደጉዋቸው።

ባሏ በሴቶች እኩልነት እና ለሁሉም ትምህርት መማር እንዳለበት ያምን ነበር. እህቱ በወሊድ ጊዜ ስትሞት ሦስት ትናንሽ ሴት ልጆቿን ወደ ቤት አመጥቶ የቤተሰብ አባል እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ባሏ የሞተባት አማቷ በየአመቱ ሩዝ በመሸጥ ገንዘቡን ለቤተሰብ አባላት ታከፋፍላለች። አማቷ ለሁሉም ሴቶች እኩልነት በማመን ገንዘቧን በፆታ፣ በእድሜ እና በግንኙነት ሳትገድብ በእኩልነት ለምራቷ፣ ለወንድ ልጇ ወንድና ሴት ልጆች፣ ለሟች ሴት ልጅ ልጆች ታካፍላለች።

bubble

Mother

ምንም እንኳን እናትየዋ ስለሴቶች እኩል አያያዝ ብትማርም በህንድ ማህበረሰብ የተንሰራፋውን ባህል ተቀብላለች። ይህ አድሎአዊ ባህል ህብረተሰቡን በሰብአዊነት ደረጃ ብቻ ሳይሆን ህንድን እስከ 4 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት አስከፍሏታል።

የማሪ አድሏዊና ወንጀለኛ ወንድሞች

ሦስቱ ወንድሞች ከሰው እንደሚበልጡ ያምናሉ። የማሪን ንብረት በሙሉ በስግብብነትለራሳቸው ይፈልጋሉ። እናትየዋ በልጆቿ እጅ ያለች አሻንጉሊት ነች። እንድትፈርም የሚነግሯትን ማንኛውንም ነገር ሁሉ ትፈርማለች።

bubble

brothers

አድሏዊ የሆኑት ወንድሞቿ የአባታቸውን የእርሻ መሬት በሕገወጥ መንገድ ሸጡ ከዚያም በተጨማሪ ማሪ የሚገባትንም ድርሻ በስግብግብነት ወስደዋል

bushes

ማሪ የከፍተኛ ትምህርቷን ለመከታተል ወደ ሌላ ከተማ ስትሄድ ስግብግብ የሆኑ ወንድቿ የአባትን የእርሻ መሬት በመሸጥ እና የሷንም የሚገባትን የንብረት ድርሻ ወስደዋል። በህገ ወጥ መንገድ መሬቱን ለህንፃዎች በመከፋፈል በትልቅ ትርፍ ሸጠዋል።

ማሪ

mari

ማሪ ትምህርቷን እንደጨረሰችወደ አባቷ ቤት ተመልሳ በከፊል በተሰራው እና ባዶ በሆነው የቤቱ የላይኛው ክፍል መኖር ጀመረች።

ወንጀለኛ ወንድሞቿ ማሪን በኬሮሲን ለማቃጠል ሞከሩ

brother1
burner
brother2

ምሽት ላይ ወንድቿ ማሪን በኬሮሲን ለማቃጠል ሞከሩ።ወንዶች ስለሆንን እና የበላይ ስለሆንን ይህ መብታችን ነው ብለውም ያምኑም ነበር ። እናትየው ይህንን አሰቃቂ ክስተት ብታይም እና ምንም አላደረገችም።

ሆኖም ማሪ አመለጠች። እኩለ ሌሊት ላይ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ የወንድሞቿን የግድያ ሙከራ ለፖሊስ አሳወቀች። በመጨረሻም ፖሊስ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ልኳል። በሚቀጥለው ቀን የማሪ እናት ፖሊሶች ማሪ ቤት ሳትኖር እንደመጡ ነገረቻት ። እናትየዋ ማሪን ከመንገድ ማዶ ያለው ጎረቤት ፖሊሶች ለምን ቤታቸው እንደመጡ ጠየቀን ብላ ተቆጣቻት። ማሪንም "ይሄን ያደረግሽው አንቺ ነሽ!" በማለት በመወንጀል ከዚያም ማሪ ጉዳዩን ከፍርድ ቤት እንድታቋርጥ ደጋግማ ነገረቻት። በእርግጥ ማሪ ያን አላደረገችም። ከዓመታት በኋላ ማሪን ፍርድ ቤቱ ስለ እሷ ጉዳይ አነጋግሯት አያውቅም። ወንጀለኛ ወንድሞቿ በሰሩት ወንጀል ፈጽሞ አልተቀጡም። ለማሪም ፍትህ አልነበረም።

ወንጀለኛ ወንድሞቿ ማሪ እንድትሞት ይፈልጋሉ

bubble

brothers

ወንጀለኛ ወንድሞቿ ማሪን በቢላ ሊወጉ ሞከሩ ከዛም ያለማቋረጥ ያስቸግሯት ነበር

knife
tap

ወንጀለኞቹ ወንድማሞች ማሪን በቢላ ሊወጉ ሞከሩ። ማሪን ያለማቋረጥ ስፍር ቁጥር በሌላቸው መንገዶች ያሰቃዩዋት ነበር ለምሳሌ በሯ ላይ በመሽናት እና የውሃ አቅርቦቷን በመቁረጥ ነበር። እኩለ ሌሊት ላይ ማሪ ከጓሮው የቧንቧ ውሃ ወደ ደረጃው ማውጣት አለባት። ማሪ ለፖሊስ ቅሬታዋን ቀጠለች ነገር ግን ወንጀለኞቹ ለፖሊሶች ጉቦ ይሰጡ ስለነበር ምንም አላረጉም ።

ወንጀለኛ ወንድሞቿ በራሷ ሴት ልጅ ከምትታገዝ ተከታታይ ገዳይ ጋር በማሴር ማሪ ጥቃት እንዲደርስባት አድርገዋል ።የወንጀለኛዋ ባሏም ያለማቋረጥ ማሪን ይከታተላታል።

employee
daughter
son
hammer

ወንጀለኛ ወንድሞች አላግባብ በመጠቀሟ ከሥራ ከተባረረች ሴት የባንክ ኦፊሰር ጋር አሴሩ። እሷም ተከታታይ ገዳይ ነበረች። በሴት ልጇ በእርዳታ ብዙ ሰዎችን ታጠቃለች በዛም በቲቪ ትዋቂ ሆነች ።

ማሪ በምትኖርበት ፎቅ ላይ ኬሮሲን ለማቃጠል ከተሞከረ ከአንድ ዓመት በኋላ ይህች ሴት በሴት ልጇ በመታገዝ በመዶሻ በማስፈራራት ንብረቷን ዘረፈች። የታችኛው ክፍል የወንድማማቾቹ ቤት ነበር። ማሪ ተደባድባ እራሷን አተረፈች። አጥቂዋ ከሄደች በኋላ ማሪ በጸጥታ ወደ ጎዳና ተከተለቻት። ከመንገዱ ማዶ የሚገኝ የትምህርት ተቋም ተማሪዎች ለምሳ ዕረፍት እየወጡ ነበር። ልጆቹም አጥቂዋን ከነጦር መሳሪያዋ ይዘው እቃዎቹን ተቀብለው ፖሊስ እስኪደርስ ያዙአት። ፖሊስም ጉዳዩን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልኳል። ከዚያ በኋላ ማሪ ለፖሊስ ቅሬታ ብታቀርብም የተከታታይ ገዳይ ባሏሳያቋርጥ ማሪን አሳደዳት። ከዓመታት በኋላ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እልባት አላገኘም እና እንደገናም ለማሪ ፍትህ አልተገኘም።

ወንጀለኛ ወንድሞቿ ማሪን ለመግደል ወንጀለኛ ከሆነው የማሪ ማርሻል አርት አስተማሪ ጋር አሴሩ ።

attacker
mari

ማሪ ራሷን ለመከላከል ማርሻል አርት መማር ጀመረች። ወንጀለኞቹ ወንድማሞች ማሪን ለመግደል ከማርሻል አርት አስተማሪ ጋር ተባበሩ። ማሪ ከአስተማሪው የግድያ ሙከራ ተረፈች ግን ማርሻል አርት መማር ማቆም ነበረባት።

country
House

ወንጀለኛ ወንድሞቿ በሕገ-ወጥ መንገድ የአባታቸውን እናት የሩዝ ማሳን እና ቤት ሸጡ እናም ማሪን የሚገባትንም ድርሻ በስግብግብነት ወስደዋል

ወንድማሞቹ የአባታቸውን እናት የሩዝ ሜዳና ቤት በመሸጥ ማሪ የሚገባትን የውርስ ንብረት በስግብግብነት ወሰዱ። እንደገና ማሪ በውልደት ያገኘችውን መብቷን ተነፈገች። ማሪ ከንብረቱ ድርሻዋ ትምህርት በሌለበት መንደር ውስጥ ትምህርት ቤት መገንባት ፈልጋ ነበር።

ወንጀለኛ ወንድሞቿ የማሪን ኮከብ ወደ አስደናቂው ኮከብ ቆጣሪ ላኩ

ሳጅ ብህሪጉ ሳፕታሪሺ,ይ ኮከብ ቆጠራ የመጀመሪያ አዘጋጅ። ፎቶ ፡ ሽርማቲ ሳቲሽ ጃናርዳን ሻርማ ፣ ዶር ፓንዲት ራማንጁ ሻርማ ፣ዊኪፒዲያ

ወንድሞች በኒው ዴሊ ውስጥ አንድ አስደናቂ ኮከብ ቆጣሪ እንደሚኖር አወቁ ከዛም የማሪን ኮከብ ላኩለት።

አስደናቂው ኮከብ ቆጣሪም ስለ ማሪ ዝርዝር መረጃ ላከላቸው፡ “ይች ሴት የራሷን ስራ ምሰራ ሴት ነች።ሰውን ምታስቸግር ሴት አይደለችም።እሷ ሳትሆን በዙሪያው ያሉት ሰዎች ናቸው መስተካከል ያለባቸው ሲል ተናግሯል።”

የማሪ ሳይንሳዊ ምርምር ለማድረግ ያላት ህልም

airplane

የማሪ ህልም ሳይንሳዊ ምርምር ማድረግ ነበር። ለእንደዚህ አይነት ስራ በሳይንስ የላቀ ሀገር ያስፈልጋታል። ምርምር ለማድረግ ወደዚያ ሀገር ሄደች። እውቀቷን ለሰዎች ሁሉ መሻሻል በማበርከት ለሌሎች የበለጠ ማድረግ እንደምትችል ተሰማት።

ማሪ የእሷ ጉዳይ ሌሎች ህንዳውያን ሴቶች በህይወት ዘመናቸው እኩልነትን እንዲጠይቁ ሊያነሳሳ እንደሚችል ተስፋ አድርጋለች።

የማሪ ቅድመ አያቶቿን ለማክበር የምታደርገው ጥረት እና ምኞታቸውን ለማሟላት የምታደርገውበጎ አድራጎት

bubble

mari

ማሪ በቤተሰቧ ወይም በባህሏ መገለልን አልፈቀደችም። ሁሉንም ሰዎች የሚጋጥሙትን ችግሮች በበጎ አድራጎት ለመፍታት ፈቃደኛ ነበረች እናም ለሌሎች አሳቢ ነበረች ። በዋረን ቡፌት፣ እና ቢል ጌትስ እና ሜሊንዳ ፈረንሣይ የተሰጡትን ምክሮች ትኖር ነበር። ማሪ የአልፍሬድ ኖቤልን የህይወት ታሪክ ስታነብ ከ እርዳታ እና በጎ አድራጎት ጋር በተያያዘ ሀሳቧን የምትገልጽበት አነቃቂ መንገድ አገኘች። የእርሷ እምነት በአማኑኤል ኖቤል ቃል ውስጥ ተገልጧል. እነዚህን ጉዳዮች በመፍታት በ 21 ኛው ክፍለ ዘመን በሴቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይ ባሉ ሰዎች ላይ ትልቁን አደጋ እየፈታች ነበር።

ማጠቃለያ

የማሪ የእናቷ እናት ለማሪ እውነቱን ተናገረች

የማሪ ጎበዝ የሆነችው የእናቷ እናት ባልተለመደ ሁኔታ ከፍተኛ ስሜታዊ ብልህነት [ስብ] ነበራት። ከውስጥ እና ከውጭ የሰዎችን አእምሮ ታውቃለች። ለሰዎች ልባዊ ፍላጎት ነበራት።

Pinoccio

ፒኖኪዮ፣ የእውነት የለሽነት ምልክት። ምስል፡ ኤንሪኮ ማዛንቲ (1852-1910)

የእናት እናቷ፣ “እናትሽ በጣ ትዋሻለች።
ማሪ፣ “አያቴ፣ የሆነ ነገር ከተናገረች፣ አንድ ሰው ይሰማዋል፣ “አዎ፣ እንደዛ ነው።
የእናቷ እናት፣ “አዎ፣ እንደዚህ ያለ የሚያምን፣ መዋሸት መንገዱ ነው።

የማሪ እናት በጣም ከመዋሸቷ የተነሳ ከሃያ አመት በኋላ እንኳን ያቺ ሴት ዋሽታለች ብሎ ወደ አእምሮው አይመጣም።

Brahma

ብራህማ ፣ እግዚአብሔር እንደ ፈጣሪ። ምስል: የሂንዱ ብሎግ

የማሪ እናት እናት የሰዎችን አእምሮ በማሻሻል ረገድ ጎበዝ ብትሆንም “ብራህማ [ፈጣሪን የተመሰለው] ራሱ ወደ ምድር ቢወርድ እንኳን ብራህማ እናትሽን ሊያስተካክልላት አይችልም” ትላለች።

ተከታታይ ገዳይ የሆነችው እና ሴት ልጇ ለዓመታት ብዙ ሰዎችን ለመግደል ሙከራ አድርገዋል


ተከታታይ ገዳይ የሆነቸው እና እያደገች ያለችው ሴት ልጇ ለዓመታት ብዙ ሰዎችን ለመግደል ሞክረዋል። ከበርካታ አሥርተ ዓመታት በኋላ እናትየው በመጨረሻ ጥፋተኛ ሆና የሰባት ዓመት እስራት ብቻ ተፈረደባት። ከሶስት አመት በኋላ እናቷ በመሞቷ ምክንያት በይቅርታ ላይ እያለች እራሷን አጠፋች።

የወንጀለኛዋ ያደገች ሴት ልጅ በህንድ ህግ እንደተገለጸው 'የእድሜ ልክ እስራት' ተፈርዶባታል።

ሁለቱም ትልቅ ዜና ተሰርቶባቸዋል። በህንድ ውስጥ እንደዚህ ያሉ ወንጀለኞች ጥፋተኛ ሆነው መገኘታቸው ለዓመታት ብዙ ሰዎችን ለመግደል ሙከራ ሲያደርጉ እንደነበር ሲታሰብ አስገራሚ ነው።

በማሪ ጉዳይ ወንጀለኛ የሆኑት እናት እና ሴት ልጇ ወንጀለኞች ቢከሰሱ እና ቢታሰሩ ሌሎች ብዙ ተጎጂዎችን እንደ ግድያ ሙከራ ካሉ የወንጀል ተግባሮቻቸው ይታደጋቸው ነበር።

የወንጀለኛ ወንድማሞች ስግብግብነት

fundraiserወንጀለኛ የሆኑት ስግብግብ ወንድማሞቹ በከተማ የሚገኘውን የእናታቸውን እናት ትልቅ ቤት በመሸጥ የተገኘውን የገንዘብ ድርሻ ለራሳቸው ወሰዱ። የማሪ የእናት እናት ወንድ አያት በትውልድ ከተማው በወንዞች መጋጠሚያ በሆነው በወንዝ ዳርቻ ላይ የሰዎች የሞት መታሰቢያ ሥነ ሥርዓቱን የሚያከናውኑበት ሕንፃ መገንባት እንደሚፈለጉ ደጋግመው ይናገሩ ነበር። ማሪ ገንዘቡን የክርስትና አያቷን ፍላጎት ለማሟላት ልትጠቀምበት ትፈልግ ነበር።/p>

funds1 እናትየዋ ከሞተች በኋላ ወንጀለኛ ስግብግብ ወንድማሞቹ ሁሉንም የእናትየውን ገንዘብ፣ ወርቅ፣ ብር ወዘተ ለራሳቸው ወስደዋል።ማሪ ገንዘቡን የእናቷ አባትን [የማሪን እናት የክርስትና አባት] ፍላጎት ለማሟላት ልትጠቀምበት ትፈልግ ነበር።

ከዛም ሀብታሞች፣ ወንጀለኞች፣ ስግብግብ የሆኑት ወንድማማቾች የአባታቸውን የእርሻ መሬት እና የአባታቸውን እናት የእርሻ መሬት እና ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሸጡ። የእናታቸውን እናት ትልቅ ቤት በመሸጥ የተገኘውን የእናታቸውን የገንዘብ ድርሻ ለራሳቸው ወስደዋል። እናታቸው ከሞተች በኋላ የእናቸውን ገንዘብ፣ ወርቅ፣ ብር ወዘተ ለራሳቸው ወስደዋል በስግብግብነትም ማሪን የሚገባትን ድርሻ ይዘዋል።

Discover Your Abilities and Aspirations!

$10 $25 $50 $100 Other
Tax Exempt 501(c)3 Non-Profit Organization
Any Currency

“One comes to be of just such stuff as that on which the mind is set” - Maithri Upanishath, VI.34:3

“…the peace that is found in libraries and laboratories…” - Louis Pasteur
Contact Us E-Mail: Ganga@GangaLibrary.org
Ganga library non-profit 501(c)(3) org. Contributions tax deductible. IRS Tax ID 46-2892728

Copyright © 2022 Ganga Library Inc.   All Rights reserved.;